ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት 6 ወራት ከ25 ቢሊየን በላይ ብር ማግኘቱን አስታወቀ።

የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በተቋሙ ግማሽ ዓመት አፈጸጸም ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።

ወይዘሪት ፍሬህይወት በዚህ ጊዜ እንዳሉት ባለፉት 6 ወራት 25 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል።

ገቢው ካለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጸጸር በ12.3 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ተቋሙ በአጠቃላይ 50.7 ሚሊየን ደንበኞች እንዳሉት ተገልጿል።

ካሉት ደንበኞች ውስጥ 48.9 ሚሊዮኖቹ የሞባይል ደንበኞች ሲሆኑ 23 ነጥብ 5 ሚሊዮን ደግሞ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ናቸው።

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *