ውቅሮ ፣አዲግራት እና ደገ ሀሙስ አካባቢዎች የስልክ አገልግሎት መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።

የተቋሙ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንዳሉት በትግራይ ክልል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት የቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደገና ለማስጀመር ጥረቶች ቀጥለዋል ብለዋል።

በአዲግራት፣ውቅሮ እና እደጋ ሀሙስ አካባቢዎች ኔትወርክ አገልግሎት ተጀምሯል ብለዋል።

በሌሎች አካባቢዎችንም የስልክ አገልግሎት ለማስጀመር የጥገና ስራዎችን እየሰራን ነውም ብለዋል።

የሳይበር ጥቃት ሙከራ በስራችን ላይ ችግር ሆኖብን ነበር ነገር ግን ኔትዎርካችን ሳይነካ መክተን አልፈናል ሲሉም ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።

በመቅደላዊት ደረጀ።
ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.