125ኛው የአድዋ በዓል የካቲት የአድዋ ወር በሚል ከየካቲት 1 ቀን ጀምሮ እንደሚከበር የባህል እና ቱሪዝም ሚንስቴር አስታወቀ።

ሚንስቴሩ በበዓሉ አከባበር ዙሪያ ከብዙሀን መገናኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር በአዲስ አበባ እየመከረ ነው።

በዚህ ጊዜ እንደተገለጸው 125ኛው የአድዋ በዓል ከየካቲት 1 ቀን እስከ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።

የአድዋ በዓል በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎችን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች በሚገኙበት ቦታ ሁሉ አንድነታችንን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል ተብሏል።

ከበዓሉ አከባበር ዝግጅቶች መካከልም በአገሪቱ ባሉ ሁሉም ወረዳዎች የአድዋ ድል መታሰቢያ ይዘጋጃል፣

የአድዋ ዘማቾች ጀግኖች ስም መታሰቢያ ይዘጋጃል፣

አድዋን ለአባይ የተሰኘ ለህዳሴው ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይዘጋጃል፣

ድሉ የመላው ኢትዮጵያውያን ድል እንደመሆኑ የአድዋ ጀግኖች የሚታወሱበት በዓል እንዲሆን በርካታ ዝግጅቶች እንደተዘጋጁ በመድረኩ ተጠቁሟል።

የአድዋ ድል ጣልያን ከ125 ዓመት በፉት ወይም በ1888 ዓ.ም ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት በሰሜን በኩል ወደ ግዛቷ በመዝለቅ ያደረገችውን ወረራ በመመከት አገርን ነጻ ያወጡበት ድል ሲሆን ይህ ድል ለመላው ጥቁር ህዝብ የእናሸንፋለን መንፈስን ያላበሰ ዓለም አቀፍ ድል ነው።

የበዓሉ ማጠቃለያ በዓል “አድዋ የህብረ ብሔራችን አርማ “በሚል መሪ ሀሳብ በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ ሶሎዳ ተራራ ላይ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ይከበራል።

በሳሙኤል አባተ
ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.