ለአዲስ አበባ ነዋሪ ከ60 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ቢያስፈልገውም እየቀረበ ያለው ግን 25 ሚሊዮን ሊትር በታች እንደሆነ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ የምግብ ዘይት እጥረት እና የዋጋ ንረት ነዋሪውን እየተፈታተነው እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

የንግድ እና ኢንዱስትሪ ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር አንድ ላይ በመሆን በሰራው ጥናት መሰረት የኮሮና ወረርሽኝ በኢትዮጲያ መከሰቱ ከተነገረበት ጊዜ አንስቶ ከ330 – 360 ብር ይሸጥ የነበረው የምግብ ዘይት እስከ 450 ብር እየተሸጠ ነው ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድ ኢንስፔክሽን እና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ካሳዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ከቀረጥ ነፃ የሚገቡ ምርቶች የመሸጫ ዋጋን ዙርያ የቁጥጥር ስራን የሚያግዝ የመሸጫ ዋጋ ማዕቀፍ ይቀመጣል ተብሏል።

እንደእርሳቸው ገለፃ አብዛኛውን አስመጪዎች የክልል ንግድ ፍቃድ የያዙና ክምችታቸው ከአዲስ አበባ ውጪ እንደሆነ እና እነሱን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ በመሆኑ እነርሱ ላይ ክትትል ማድረግ ይጀመራል ብለዋል።

ከዛም በተጨማሪ በመንግስት ድጎማ የሚቀርበው የፖልም ዘይት ላይ በተደረገው ማጣራት ከፍተኛ ህገ – ወጥነት ታይቷል ብለዋል።

በማጣራት ሂደቱ በአዲስ አበባ 134 ሸማች ማህበራት በ114 ወረዳዎች ላይ ለህዝቡ ማድረስ ላይ ውስንነት እና ህገ – ወጥነት እንዳለው መገምገሙን ገልጿል።

በዚህም ለአዲስ አበባ ነዋሪ ለማድረስ ከታቀደው 60.6 ሚሊዮን ሊትር ቢሆንም ማቅረብ የተቻለው ግን 24.8 ሚሊዮን ብቻ ነው።

አፈፃፀሙም ሲታይ 40.8 በመቶ ብቻ ነው።

በረድኤት ገበየሁ
ጥር 14 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *