በመቀሌ ከተማ ከ350 ሚሊዮን በላይ ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የህክምና ግብዓቶች ክምችት እንዳለ የፌደራል መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ አስታወቀ።

በትግራይ ክልል የመድሀኒትና የህክምና ግብዓቶች ወደ ጤና ተቋማት ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑንም ተነግሯል።

ኤጀንሲው እንዳስታወቀው ከሆነ በትግራይ ክልል ለ47 ጤና ተቋማት 18 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የህክምና ግብዓቶችን በቀጥታ ወደ ክልሉ በመድረስ የማሰራጨት አገልግሎት ማከናወኑን አስታውቋል።

ቅርንጫፉ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 47 የጤና ተቋማት ግብዓቶቹን በቀጥታ ያሰራጨ ሲሆን በተለይም በመቀሌ ለሚገኙ 4 ሆስፒታሎች ለዉቅሮ፣ ሀውዜን፣ አዲግራት፣ አክሱም ቅድሰት ማርያም፣ ኮረምና ሌሎች ሆስፒታሎች መድሃኒቶችን አሰራጭቻለሁ ብሏል።

በሌላ በኩል በሰሜን እና በምዕራብ አንዲሁም በማዕከል በሚገኙ የኤጀንሲው ቅርንጫፎች የመደበኛ እና የጤና ፕሮግራም መድሀኒት የህክምና ግብዓቶችን ለሁመራ፣ ለአላማጣና ለሌሎችም የጤና ተቋማት ግብአቶቹ በመሰራጨት ላይ ናቸው ተብሏል።

በአሁኑ ወቅትም በኤጀንሲው መቀሌ ቅርንጫፍ ከ350 ሚሊዮን በላይ ብር ዋጋ ያላቸው የመደበኛ እና የጤና ፕሮግራም የህክምና ግብዓቶች ክምችት መኖሩን ኤጀንሲው አስታውቋል።

መድሀኒቶቹም ለእናቶች እና ህፃናት ጤና ፣ ለስኳር፤ ለደም ግፊት ህመምተኞች፣ ለፀረ ወባ፣ ለሳንባ ነቀርሳ ፣ለኤች አይቪ ኤድስ ህሙማን ህክምና የሚውሉ ናቸው ተብሏል።

በየውልሰው ገዝሙ
ጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *