በአዲስ አበባ የመኪና ጎማ መሸጫ ዋጋ እስከ 1 ሺህ 500 ብር ጭማሪ አሳይቷል።


አሽከርካሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በአገር ውስጥ የተመረቱትም ሆኑ ከውጭ የገቡ የመኪና ጎማ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እንዳሳዩ ነግረውናል።
አሽከርካሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ የዋጋ ለወጡ በአጭር ጊዜ ከመሆኑም በላይ በአንዴ ከ800 አስከ 1 ሺህ 500 ብር ድረስ ነው ብለዋል፡፡

የዋጋ ጭማሪው ለምን ሆነ ብለው ሻጮችን ስንጠይቅው የዶላረ እጥረት ነው ከማለት ውጪ ሌላ ተጨማሪ ምክንያት አልሰማንም በዚህም ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብተናል ሲሉ አሽከርካሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ያነገርናቸው የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ግዛው ተክሌ በበኩላቸው ተቋማችን በዋናነት መሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ ማለትም ነዳጅ፣ ስኳር ፣ ዘይት የመሳሰሉት ላይ ክትትል እናደርጋለን ብለዋል፡፡

ከዛም በተጨማሪ የምርቶች መሸጫ ዋጋ ተጋነነ የሚባል ለውጥ ካለው ደግሞ የገበያ ጥናት እንሰራለን ነገር ግን ይህም ቢሆን ለማረጋጋት ካልሆነ በቀር ዋጋ መወሰን አንችልም ሲሉ አማካሪው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
ጉዳዩ የሸማቾች ባለስልጣንን ነው የሚመለከተው ሲሉም አማካሪው አክለዋል።

የፌደራል የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለ ስልጣን የህዝብ ግንኙኘት ዳይሬክተር አቶ አልቃድር ኢብራሂም በበኩላቸው ስለ ጉዳዩ ተቋማቸው ምንም አይነት መረጃ እንደሌለው ተናግረዋል።
ተቋማቸው ይህንን ለማጣራት እና ወደ መፍትሄው ለመሄድ የችግሩ መንስዔ ምንድነው? አምራቾችሰ ገበያውን በበላይነት ካለ አግባብ ተቆጣጥረዋል ወይ? የሚለው መታየት አለበት ብለዋል፡፡

አቶ አልቃድር ጨምረውም በጉዳዩ ዙሪያ ክትትል እንደሚያደርጉ እና የችግሩ መንስዔ ከታወቀ እና የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ካለ ተጠያቂ ለማድረግ ይሰራል ብለዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
ጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *