ቼልሲ ፍራንክ ላምፓርድን አሰናበተ፡፡

ቼልሲ አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድን ከ18 ወራት ቆይታ በኃላ አሰናብቷል፡፡

የቀድሞ የክለቡ የመሀል ሜዳ አቀጣጣይ እንደዚሁም ያሁኑ የክለቡ አሰልጣኝ ሆኖ በመስራት ላይ የነበረው ፍራንክ ላምፓርድ ከአሰልጣኝነቱ መነሳቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

የ42 አመቱ ፍራንክ ላምፓርድ በሶስት አመት ኮንትራት ነበር በ2019 የቀድሞ የክለቡ አሰልጣኝ የነበሩትን ማውሪዚዮ ሳሪን በመተካት ክለቡን ተቀላቅሎ የነበረው፡፡

ባለፈው ሳምንት በሌስተር ሲቲ የ2 ለዜሮ ሽንፈት ለአሰልጣኙ መባረር ምክንያት እንደሆነ ነው የተነገረው፡፡

ያለፈው አመት ክለቡ ቼልሲ አራተኛ ሆኖ የውድድር አመቱን ቢጨርስም ጥሩ ተስፋ በቡድኑ ውስጥ ማስቀመጥ ችሎ ነበር፡፡

ቼልሲ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አንዱን ብቻ ያሸነፈ ሲሆን የአሰልጣኙ መሰናበት በርካታ የስፖርት ሚዲያዎች በፊት ገጻቸው አውጥተውታል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *