የአዲስ አበባ ከተማ ሁለንተናዊ የሆነ የትራንስፖርት ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችል የአስር አመት እቅድ መታቀዱን እና እቅዱም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ቀርቦ እንደፀደቀ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኮሚውኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አረጋዊ ማሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በተለያዩት እቅዶች ላይ አምስት ዋና የሚባሉ ችግሮች በአስር አመት እቀድ በዋናነት እንደሚተገበርባቸው ተገልጿል፡፡ከእነርሱም መካከል ከ2011 ሃምሌ ወር በፊት የትራንስፖርት ፈንድ የተባለ ፅህፈት ቤት የነበረ ሲሆን፣ እርሱ ፅህፈት ቤት ታጥፎ አሁን ወደ ሌላ አደረጃጀት መግባቱን ተከትሎ ‹‹ ተቋሙ ከራሱ የሰበሰበውን ገንዝብ ለራሱ የሚያውል በመሆኑ እሱን ተቋም መልሶ በማቋቋም አንዱን ችግር ለመቅረፍ ታቅዷል›› ሲሉ አቶ አረጋዊ ነግረዉናል፡፡
ከዛም በተጨማሪም ከ2013 አስከ 2022 ድረስ ከሚተገበሩት መካከል የመንገድ መሰረተ ልማት አውታር ካለው የትራንስፖርት ፍላጎት ጋር አለመጣጣሙን ገልፀው ፣ የመንገድ መሰረተ ልማት ፣ የእግረኞች መንገድን ጨምሮ ማስፋት ፣ የብዙሃን ትራንስፖርቶችን፣ የአውቶቢስ ተርሚናሎችን መጨመር እና እነርሱንም ማስተናገድ እንዲቻል ለማድረግ እንደሚሰራ በእቅዱ ተካቷል ብለውናል ፡፡
በከተማዋ ላይ አሁን ባጠቃላይ እስከ 13 ሽህ የሚደርሱ ተሽከርካሪዎች ቢኖሩም፣ ከዚህ ውስጥ የብዙሃን ትራንስፖርቱ ማለትም አንበሳ ባስ ፣ ሸገር ባስ ፣ ፐብሊክ ሰርቪስ ሰጪ ተሸከርካሪን ጨምሮ ከ 1 ሺህ 100 እንደማይበልጥ ገልፀው አሁን ላይ እርሱን ለማሻሻል እንደሚሰራ ተናግረዋል ፡፡
የክትትል እና የቁጥጥር ስራው ላይም በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ እንደሚሰራ ተቀምጧል ብለዋል፡፡ሌላኛው ችግር ሆኖ የተቀመጠው የትራንስፖርት ፕላኒንግ እና ልማትን ከከተማዋ ማስተር ፕላን ጋር ማስተሳሰር አለመቻሉ ነው ያሉት አቶ አረጋዊ፣ ዋነኛ ምክንያቱ ደግሞ የወሰን ማስከበር ሂደቱ ነው ብለውናል፡፡
አክለውም የትራንስፖርት ዘርፉ በሚፈልገው ባለሙያ እየተመራ እንዳሆነ ገልፀው፣ የትራንስፖርት ዝርፉን ለማሻሻል ከከፍተኛ ትምህርረት ተቋማት ጋር በማስተሳሰር ለመስራት በትኩረት አቅጣጫው ላይ መቀመጡን ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
በረድኤት ገበየሁ
ጥር 18 ቀን 2013 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን











