በአዲስ አበባ ድንገት በተከሰተ የእሳት አደጋ የ ሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ።

የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በትላንትናው እለት በደረሰ ድንገተኛ የእሳት አደጋ የሁለት ሰው ህይወት ማለፉን ገልጿል፡፡

አደጋው የደረሰው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ቦኖ ውሃ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ በቀበሌ መኖሪያ ቤቶች ላይ ነው፡፡

በተከሰተው ድንገትኛ የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ታውቋል፡፡

ህይወታቸው ያለፈው አንድ አረጋውያንና አንድ ወጣት ናቸው፡፡

እንደዚሁም አንድ ወጣት ህክምና ተሰጥቶት ወደ ቤት መመለስ መቻሉንና በአደጋውም ሁለት ቤቶች ሙሉ በሙሉ መቃጠላቸውንም ነው ያስታወቀው፡፡

የአደጋው መንስኤ በፖሊስ በመጣራት ላይ የሚገኝ ሲሆን በአደጋው ምን ያህል ንብረት ለውድመት እንደተዳረገ እና ምን ያህል ንብረት ደግሞ ማዳን እንደተቻለ በመጣራት ላይ ነው፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *