በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በመጨመሩ ምክንያት የአስከሬን ሳጥን ዕጥረት ማጋጠሙ ተገለጸ።


በሃገሪቱ የሚገኙ የሬሳ ሳጥን አዘጋጆች በየእለቱ እየተመዘገበ ያለው የሟቾች ቁጥር ካለው የአስክሬን ሳጥን ጋር የሚመጣጠን እና ለማዘጋጀትም መቸገራቸውን ገልፀዋል፡፡

በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ክፉኛ ከተጠቁ አገሮች መካከል አንዷ የሆነችው ደቡብ አፍሪካ አሁን ደግሞ በአዲስ የኮሮና ቫይረስ ዝርያ የሚሞቱባት ዜጎቿ ጨምሯል።

ሃገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአዲሱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እጅግ እየተጠቃች ሲሆን እስካሁን ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዚሁ ቫይረስ ሲያዙ ከ40 ሺ 800 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።
ይህም ብቻ ሳይሆን በዚሁ ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ዜጎች አስከሬን መከማቸቱንና ሁኔታው በዚሁ ከቀጠለ የሬሳ ማከማቻዎች ቦታም ሊጠፋ እንደሚችል ተነግሯል ፡፡

ተመራማሪዎች የበለጠ ተላላፊ ነው ተብሎ እየተነገረ ያለው አዲሱ የቫይረስ ዝርያ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን አስታውቀዋል ፡፡

የሃገሪቱ የሬሳ ሳጥን አምራቾችም እለት ተእለት የሟቾች ቁጥር መጨመሩ ጫናው እየተሰማቸው እንደሆነ አስከሬን ሳጥን ለማምረት ሌት ተቀን እንቅልፍ አጥተው እየሰሩ ነው ሲል ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል

በየውልሰው ገዝሙ
ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *