የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ቻናሎች ወደ ኢትዮ ሳት መቀየራቸው ተከትሎ የዲሽ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል፡፡

ከሰሞኑ በርካታ የቴሌቪዥን ቻናሎች ወደ ኢትዮ ሳት መቀየራቸው ተከትሎ የዲሽ ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ነው የተነገረው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም በተለያዩ የዲሽ እቃ መሸጫ ሱቆች ተዘዋውሮ በተመለከተበት ሰአት በዲሽ እቃዎች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ መኖሩን ታዝቧል፡፡

በዋናነት ኢትዮ ኤፍ ኤም በጎጃም በረንዳ፤ በመርካቶ። በሶማሊያ ተራ የዲሽ መሸጫ ሱቆችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል፡፡

እንደማሳያ ከአንድ ወር በፊት ኤች ዲ ላይፍ ስታር ከ650 እስከ 700 ይሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ እስከ 1000 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

እንዲሁም ሱፐር ስታር ኢሮ ቦክስ እና ኤል ኢጂ 700 የነበረ ሲሆን አሁን እስከ 1 ሺህ 100 ድረስ እየተሸጠ ይገኛል፡፡

የዲሽ ዋጋ በተመለከተም ባለ 60 ሳህን 600 ብር የነበረ ሲሆን አስከ 850 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

ባለ 90 ሳህን ደግሞ 700 የነበረ ሲሆን አሁን ላይ እስከ 1 ሺህ አንድ መቶ ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ኢትዮ ኤፍ ኤም መታዘብ ችሏል፡፡

እንደዚሁም የዲሽ ገመድ ዋጋም በተመለከተ ከዚህ በፊት 20 ሜትሩ አንድ መቶ ብር የነበረ ሲሆን አሁን በሜትር እስከ 6 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.