የገቢዎች ሚኒስቴር የኢ-ታክስ አገልግሎትን ይሰጥበት ከነበረው የንግድ ባንክ በተጨማሪ በሶስት የግል ባንኮች መስጠት ሊጀምር ነው።

የገቢዎች ሚኒስቴር የኢ-ታክስ አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ እና ተደራሽነቱን ለማስፋት አገልግሎቱ ከሚሰጥበት የንግድ ባንክ በተጨማሪ ሶስት የግል ባንኮች ማለትም ብርሃን ባንክ፣ ህብረት ባንክ እና ዳሽን ባንክ መስጠት ሊጀመር መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡

መስሪያ ቤቱ ለኢቲዮ ኤፍ ኤም እንደጠቆመው የኤሌክትሮኒክስ የታክስ አስተዳደር የሚፈለገው ደረጃ ላይ ለማድረስ ከባንኮችና ኢትዮ ቴሌኮም ከመሳሰሉ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ በመስራት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የአገልግሎት መጨናነቅን ለመቀነስ እና ግብር ከፋዮች ባሉበት ሆነው ግብራቸውን መክፈል እንዲችሉ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

አገልግሎቱ የኤሌክትሮኒክስ ታክስ ስርዓት (ኢ-ታክስ) ከሶስት ተጨማሪ የግል ባንኮች ጋር ስምምነት በመፍጠር አገልግሎቱን ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራው መጠናቀቁን እና ብርሃን ባንክ፣ ህብረት ባንክ እና ዳሽን ባንክ መሆናቸውንም ከመስርያ ቤቱ ኢቲዮ ኤፍ ኤም ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ ቀደም በመስሪያ ቤቱ የዚህን አገልግሎት መጀመር ይፋ መደረጉን ተከትሎ ለተጠቃሚዎች የአረዳድ ችግር እንዳይፈጥር ስልጠና ለተጠቃሚዎች ሲሰጥ እንደነበር ተገልፆ ነበር፡፡

በረድዔት ገበየሁ
ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.