የጎንደር ቤተሰብ ቃልኪዳን ፕሮጀክት በዚህ አመትም እንደሚቀጥል የጎንደር ዩንቨርሲቲ አስታወቀ ።

የጎንደር ዩንቨርስቲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በዚህ አመት ዪንቨርሲቲውን የሚቀላቀሉ አዲስ ተማሪዎች በጎንደር ከተማ ቤተሰብ እንዲኖራቸው ይደረጋል ብሏል ።

የጎንደር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አስራት አፀደወይን ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ባለፈው አመት የተጀመረው የጎንደር የቃልኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት በዚህ አመትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።

የዩንቨርስቲው የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ቤተሰባዊ ግንኙነት እንዲኖራቸው እንዲሁም የኢኮኖሚና ሌሎች ችግሮች ሲገጥማቸው ከከተመዋ ነዋሪዎች ጋር በመሆን ችግሮቻቸውን እንዲፈቱ የሚያስችል ፕሮጀክት እንደሆነም ፕሬዘዳንቱ ተናግረዋል ።

ባለፈው አመት የጎንደር ቤተሰብ የቃልኪዳን ፕሮጀክት ሲጀመር ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በጎንደር ከተማ ቤተሰብ እንዲኖራቸው መደረጉን ያስታወሱት ዶክተር አስራት በቅርቡም አዲስ ተማሪዎች ይደለደላሉ ብለዋል ።

ፕሮጀክቱ ውጤታማ እንደሆነና አዳዲስ ተማሪዎች ምንም አይነት ችግር ሳይገጥማቸው ትምህርታቸውን መከታተል እንደቻሉም ተገልጿል ።

በቅርቡ የሚጀመረውን ድልድል ጨምሮ ሁለት ዙር ድልድል እንደሚሆን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ከሁለት አመት በኋላም ሁሉም የዩንቨርስቲው ተማሪዎች በጎንደር ከተማ ቤተሰብ የሚያገኙ ይሆናል። የድልድል ሂደቱንም በተመለከተ ሁሉም ተማሪዎች እና የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በፍቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ድልድል ይከናወናል ።

ይህ ፕሮጀክት የተማሪዎቹን የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ችግር ከመቅረፉ በተጨማሪ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚነሱ ግጭቶን ለመከላከል ስለሚረዳ ሁሉም ዪንበርሲቲዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ተጠቁሟል ።

በአባቱ መረቀ
ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.