በምስረታ ላይ የሚገኘው ዳሞታ ባንክ የአክሲዮን ግዢና አከፋፈል ሂደቱም አስታውቋል።
የምስረታ ባንኩ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኤሊያስ ሎሃ በዛሬው እለት በባንኩ ምስረታ ወቅት የባንኩ መመስረት በሃገሪቱ ያለውን አነስተኛ የባንክ ቁጥርን ከፍ ማድረግ። ተደራሽነትን ጨምሮ በባንክ እድገት ውስጥ የተሻለ ደረጃን ማምጣት እና በሃገሪቱ በሚገኙ ባንኮች ያልተዳሰሱ ጉዳዮች ላይ በምርምርና በጥናት የታገዘ ባንክን ለመመስራት እቅድ መያዙን ተናግረዋል ።
በዚህም የአንድ አክሲዮን ዋጋ ብር አንድ ሺ ብር ሲሆን መግዛት የሚቻለው ዝቅተኛ የ አክሲዮን ብዛትም 50 ወይም 50 ሺ እንደሆነ ሲገለፅ አንድ ግለሰቡ ወይንም ድርጅት መግዛት የሚችለው ከፍተኛውን የ አክሲዮን መጠን ብዛት አንድ መቶ ሺ ወይንም 1 ሚሊዮን ብር ይሆናል።
እንዲሁም የአገልግሎት ክፍያው ቃል ከተገባው ጠቅላላ አክሲዮን 5 በመቶ እንደሆነም ተገልጿል።
ዳሞታ ባንክ የኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንክ የሚጠይቀውን መስፈርት በሟሟላት በአክሲዮን ሽያጭ ላይ እገኛለሁ ያለ ሲሆን ማንኛውም የባንኩ ባለቤት መሆን የሚፈልግ ግለሰብ እና ድርጅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ በሌሎች የግል ባንኮች አክሲዮን መግዛት እንደሚቻል ገልጿል።
ዳሞታ ባንክ በ500 ሚሊየን ብር መነሻ ካፒታል ወደ ስራ እንደሚገባ ያስታወቀ ሲሆን አሁን ላይ 370 ሚሊዮን የተፈረመ ካፒታል እንዳለው አስታውቋል።
በየውልሰው ገዝሙ
ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም











