ከ139 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን እንዳለዉ፣በ20/80 የቤቶች ልማት ፕሮግራም 100 ሽህ 768 ቤቶችና በ40/60 ቤቶች ፕሮግራም 38 ሽህ 240 ቤቶች በድምሩ 139 ሽህ 8 ቤቶች እየተገነቡ ይገኛሉ፡፡

ኮርፖሬሽኑ ይህን ያለዉ የግማሽ በጀት ዓመት አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት ነዉ፡፡ከዚህ በተጨማሪም 69 ነጥብ 39 ሄክታር መሬት በመረከብ 25 ሽህ 946 ቤቶችን ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት እያደረኩ ነዉ ብሏል፡፡

በ20/80 እና 40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም 51 ሽህ 229 የተገነቡ ቤቶች ለነዋሪው ማኅበረሰብ እጣ የወጣባቸው መሆኑን ኮርፖሬሽኑ ጨምሮ ገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይፋ ባደረገዉ ጥናት በከተማዋ 21 ሺህ 695 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በህገወጥ መንገድ ተይዘው መገኘታቸውን መግለጹ ይታወሳል፡፡

ከዚህ ቤቶች ውስጥ 15 ሺህ 891 ቤቶች የባለቤትነት መረጃ አልቀረበባቸውም።850 ቤቶች ደግሞ ዝግ ሆነው ሲገኙ 4 ሺህ 530ዎቹ ደግሞ ባዶ ሆነው መገኘታቸው ተነግሯል፡፡

የ10/90 ቤቶች ልማት ፕሮግራምን በተመለከተ 75 በመቶ የሚሆኑ ቤቶች የተያዙት ባልተመዘገቡና ቁጠባ ባላከናወኑ ሰዎች መሆኑን መገለጹም የሚታወስ ነዉ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.