ጆዜ እንደ ልማዳቸው ክሎፕን ወርፈዋል::

ጆዜ ሞውሪንሆ የጨዋታ ዳኞች እና የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰዎች አንዳንድ አሰልጣኞች በተጠባባቂ ወንበር ጫፍ ላይ የሚፈጽሙትን ያልተገባ ድርጊት በቸልታ እያለፉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ክሎፕ በቅርቡ ከበርንሌይ አሰልጣኝ ሾን ዳይች ጋር ወደ መልበሻ ክፍል በሚወስደው መሿለኪያ መጋጨታቸውን ለአብነት ይጠቅሳሉ፡፡

የቶተንሃሙ አሰልጣኝ እንደ የርገን ክሎፕ ዓይነት የተቀናቃኝ ቡድን አሰልጣኞች እርሳቸውን ለእገዳ እና የገንዘብ መቀጮ ሲያስጥሉባቸው የነበሩ ድርጊቶችን እየፈጸሙ ያለ ቅጣት እየታለፉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

‹‹እኔ ያልተገባ ነገር ስፈጽም ዋጋውን እከፍላለሁ›› በማለት የክሎፕ ቡድን ከቶተንሃም ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት ተናግረዋል፡፡

‹‹አንደኛው ቅጣት ቡድኔ የሚያደርገውን ጨዋታ መልበሻ ክፍል ውስጥ ሆኜ በቴሌቪዥን እንድከታተል ማድረግ ነው፡፡ ሌላኛው ከፍተኛ ገንዘብ እንድከፍል ማድረግ ነው፡፡ በአንዳንዶቹ ላይ ግን ይህ ሲፈጸም አልመለከትም›› ብለዋል፡፡

ጆዜ ማክሰኞ ዕለት 58 ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን አክብረዋል፡፡ አሁን ላይ ከምንጊዜውም በላይ የተረጋጉ መሆናቸውን እና ስክነት የሚነበብበት ውሳኔ እንደሚያስተላልፉም ይናገራሉ፡፡

አቤል ጀቤሳ
ጥር 20 ቀን 2013 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.