ምርት ገበያው ባለፉት 6 ወራት ውስጥ ከ19 ቢሊዮን በላይ ብር ማገበያየቱን ገልጿል።
ምርት ገበያው በተያዘው የ2013 በጀት ዓመት በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ነው።
ምርት ገበያው ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 19 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ዋጋ ያላቸው 320 ሺህ ቶን ምርት ማገበያየቱን ገልጿል።
ከተገበያዩ ምርቶች መካከልም ቡና፣ቦለቄ፣ሰሊጥ፣አኩሪ አተር እና ሌሎች ምርቶች እንደሆኑ በመግለጫው ተገልጿል።
ከዚህም ውስጥ 115 ሺህ ቶን ሰሊጥ ለማገበያየት ታቅዶ ከእቅዱ ከ122 በመቶ በላይ 140 ሺህ ቶን ተገበያይቷል።
በረድኤት ገበየሁ
ጥር 21 ቀን 2013 ዓ.ም











