አብን፣ መኢአድ እና ባልደራስ ፓርቲዎች ጥምረት ሊፈጥሩ መሆኑን አስታወቁ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት( መኢአድ) እና ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በቀጣዩ 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ አዲስ አበባ ጥምረት ሊፈጥሩ መሆኑን አስታውቀዋል።

የአብን ምክትል ሊቀመንበር እና የምርጫ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ የሱፍ ኢብራሒም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ሶስቱ ፓርቲዎች በጥምረት ሊሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

ጥምረቱ በሶስቱ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች መካከል ውይይት ተደርጎ ስምምነቱ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የተደረሰ ሲሆን በቀጣይ በፓርቲዎቹ የማዕከላዊ ኮሚቴ ይጸድቃል ብለዋል።

ጥምረቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤቶች የጋራ እጩዎችን ማቅረብ እና ሌሎች የፖለቲካ ስራዎችን እንደ አንድ ፓርቲ ለማከናወን ያስችላልም ብለዋል አቶ የሱፍ በቀጣይ ተመሳሳይ አላማ ካላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋርም ተመሳሳይ ጥምረት ለማካሄድ ድርድሮች በመካሄድ ላይ እንደሆኑም አቶ የሱፍ ነግረውናል።

አቶ ልደቱ አያሌው እና ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን መቀላቀላቸው ይታወሳል።

ከአንድ ወር በፊት ፓርቲያቸው በምርጫ ቦርድ የታገደባቸው አቶ ልደቱ አያሌው እና ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የፓርቲዎቻቸው አባላትን ይዘው ሕብር ኢትዮጵያ ፓርቲን መቀላቀላቸው ተገልጿል።

በሔኖክ አስራት
ጥር 21 ቀን 2013 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *