ኢትዮጵያ የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የሎጂስቲክስ ማህበርን እንድትመራ ተመረጠች።

ማህበሩን እንድትመራ መመረጧም ኢትዮጵያ የአለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ኤግዚቢሽኖች ማእከል መዳረሻ እንደሚያደርጋት ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የእቃ አስተላላፊዎችና የመርከብ ወኪሎች ማህበር (EFSAA) መስራች ወ/ሮ ኤልሳቤት ጌታዩን እንዳሉት፣ ማህበራቸው የአለምአቀፉ የእቃ አስተላላፊዎች ማህበራት ፌዴሬሽን (FIATA) ብቸኛው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ወኪል መሆኑን ገልጸዋል።

FIATA በስሩ ካሉት ክልሎች ውስት ኢትዮጵያ እንድትመራ የተደረገው የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት የእቃ አስተላላፊ ኩባንያዎች ውስጥ መሆኑን አውስተዋል።

ይህ ደግሞ ሀገራችንን አለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ኮንፈረንሶችና ኢግዚቢሽኖች ማእከል እንድትሆን የሚያስችል እድልን ይፈጠራል ነው ያሉት።

ሃላፊዋ አክለውም ሃገራችንን በማስተዋወቅ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፍሰትን የሚያመጣ ሲሆን ይህም የስራ እድልን ለማስገኘት ጥሩ አጋጣሚ ነው ብለዋል።

በዚሁ የሎጂስቲክስ ስራ ኢትዮጵያ በሎጂስቲክስ ምርጥ ተሞክሮ ካለቸው ሀገራት ልምድ ለመውስድም ያስችላታል ብለዋል።

በጅብሪል ሙሀመድ
ጥር 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *