ከ 21 ቢሊዮን ብር በላይ ከስረናል ያሉት 600 ግብር ከፋዮች ውሸታቸውን መሆኑን አረጋግጫለሁ አለ የገቢዎች ሚኒስቴር።

ባለፉት ስድስት ወራት ከ21 ቢሊዮን ብር በላይ የሀሰት ኪሳራ እና ተገቢነት የሌለው የታክስ ተመላሽ ጥያቄ መቅረቡ በታክስ ኦዲት እንደተረጋገጠ የገቢዎች ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በመንፈቅ ዓመቱ የውሸት ኪሰራ እና ተገቢነት የሌላቸው የታክስ ተመላሽ ጥያቄዎች ያቀረቡ ግብር ከፋዮች ቁጥር 642 ናቸው፡፡

ከዚህ ውስጥ 600 ግብር ከፋዮች ተቀባይነት ያላገኘ ኪሳራ 42 ቱ ግብር ከፋዮች ደግሞ ተገቢነት የሌለው የታክስ ተመላሽ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት 21 ቢሊዮን 309 ሚሊዮን 463 ሺህ 239 ብር የውሸት ኪሳራ እና ተገቢነት የሌላቸው የታክስ ተመላሽ ጥያቄዎች እንደቀረቡ በታክስ ኦዲት መረጋገጡን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል ፡፡

ግብር ከፋዮች በሀሰት ኪሳራ እንዳጋጠማቸው ሪፖርት ያደረጉትና ኦዲት በማድረግ ኪሳራው ተቀባይነት ያላገኘው የገንዘብ መጠን 21 ቢሊዮን 249 ሚሊዮን 219 ሺህ 398 ብር ነው፡፡

60 ሚሊዮን 243 ሺህ 841 ብር ደግሞ አላግባብ የታክስ ተመላሽ ጥያቄ ቀርቦበት ውድቅ እንደተደረገ ሚኒስቴር መስሩያ ቤቱ ለጣቢያችን ተናግሯል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት 149.2 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡

በሔኖክ አስራት
ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.