የሩዋንዳ ፖሊስ በመጠጥ ቤቶች ውስጥ የተገኙ ከ 100 በላይ ሰወችን አሰረ።

የርዋንዳ ፖሊስ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋትን ለመከላከል ሲባል ሀገሪቷ ያፀደቀቻቸውን፣ መሰባሰብንና አልኮል መጠጣትን የሚከልክሉ ደንቦችን ተላልፈው ተገኝተዋል ያላቸውን 113 ሰዎች እስር ቤት እንዲገቡ ማድረጉ ተሰምቷል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰውች በየመጠጥ ቤቶችና ሆቴሎች በነፃነት ሲጠጠና ሲዝናኑ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል።

ፖሊስ እንዳሳታወቀው ከሆነ ከታሰሩት መካከል 9ኙ በመንግስት የህግ አካላት ሲሆኑ የመጠጥ ቤቶች ሃላፊዎችና ማናጆሮችም ይገኙበታል ተብሏል።

በርዋንዳ በኮቪድ 19 ምክንያት የሰፈር መጠጥ ቤቶች፣ ሆሆቴሎች እንዲሁም በርካታ ሰዎች የሚሰባሰቡባቸው ቦታዎችና ተቋማት አሁንም ድረስ ዝግ እንደሆኑ ተነግሯል።

በዚህም ርዋንዳ የኮሮና ይረስ መዛመትን ለመቀንስ መመሪያዎችንና ደንቦችን በማውጣት ብቻም ሳይሆን ተፈፃሚ እንዲሆኑም ጠንከር ያለ አቋም እንዳላት ይነገርላታል።

ሀገሪቱ ምንም እንኳን እንደነዚህ ያሉ ጥንቃቄዎችንና እርምጃዎችን ብትዎድም፣ ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውና መሞታቸው ግን አልቀረም ነው የተባለው።

ነገር ግን በቫይረሱ የደረሰባት ጉዳት ከደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅና ኢትዮጵያ ካሉ በኮሮና ቫይረስ ጎዳት ከደረሰባቸው የአፍሪካ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር ግን ዝቅተኛ ሊባል ይችላል ሲል ሲጂቲኤን ዘግቧል።

በጅብሪል ሙሀመድ
የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *