ዓለም አቀፉ የቶኪዮ ኦሎምፒክ አዘጋጅ ኮሚቴ ሊቀመንበር ዮሺሮ ሞሪ ስለ ሴቶች የሰጡት አስተያየት ‹‹ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው›› ብሏል ፡፡
የ83 ዓመቱ ሞሪ ‹‹ ሴቶች ብዙ ያወራሉ፡፡ ብዙ ሴቶች ያሉበት የቦርድ ስብሰባ ብዙ ጊዜ የሚወስደው ለዚህ ነው ብለዋል፡፡ ፡፡ ዮሺሮ የሰነዘሩት አስተያየት ተገቢ አለመሆኑን አምነው ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡
ሃላፊነታቸውን በገዛ ፈቃዳቸው የመልቀቅ ምንም ዓይነት ፍላጎት እንደሌላቸው ግን ተናግሯል፡፡
የአለም አቀፉ ኦልምፒክ ኮሚቴ ሞሪ ‹‹ይቅርታ ከጠየቁ በኋላ›› ጉዳዩ እንደተዘጋ ቆጥሮት እንደነበር ገልጿል፡፡
የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር አስተያየት ተከትሎ 440 በጎ ፈቃደኞች በዝግጅቱ የነበራቸውን ተሳትፎ አቁመዋል፡፡
በአቤል ጀቤሳ
የካቲት 3 ቀን 2013 ዓ.ም











