በኮንሶ ዞን በተፈጠረው ግጭቶች ከ84 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን ኢዜማ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ በኮንሶ ዞን በተፈጠረው ግጭት ዙሪያ ያጠናውን ጥናት ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል።

ፓርቲው በዚህ ጊዜ እንዳለው በዞኑ በተፈጠሩ ግጭቶች ከ10 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች 198 ሺህ 418 ኩንታል እህል ከ100 ሺህ በላይ የግብርና መሳሪያዎች እና ቁሳቁሶች እንዲሁም ከ32 ሺህ በላይ የቤት እንስሳት ወድመዋል።

በግጭቱ ምክንያትም በአጠቃላይ 84 ሺህ 244 ዜጎች መፈናቀላቸውንም ፓርቲው አስታውቋል::

ከተፈናቀሉት ውስጥ 51 ሺ የሚሆኑት ቤት ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ እንደወደመባው ባደረግኩት ምልከታ አረጋግጫለው ብሏል ኢዜማ በመግለጫው።

በኮንሶ ዞን አሁንም ዜጎች የሰብአዊና የደህንነት ችግሮች እንደቀጠሉ ፓርቲው አስታውቋል።

የምግብ ችግር ተፈናቃች ከእንስሳት ጋር በመጠለያው አብሮ መኖር የሚሞቱ ሰዎች መብዛት የታጠቁ ሀይሎች የሚያካሄዱት ዝርፊያና ንብረት ማቃጠል አሁንም የተኩስ ልውውጥ አለመቆም ዜጎችን እያሳሰቡ ያሉ ጉዳዮች ናቸው ተብሏል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.