የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ በማይካድራ እና አካባቢውቅ ተዘዋውሮ ነዋሪዎችን ማነጋገሩን አስታውቋል።
በማካይድራው በጭካኔ የተገደሉትን የሟቾችን ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ ተቸግሪያለው ብሏል ኢዜማ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፡፡
ኢዜማ በማይካድራ የተካሄደውን ጭፍጨፋ አስመልቶ ያደረገውን ምልከታ በዛሬው እለት ሪፖርት እያቀረበ ይገኛል፡፡
ኢዜማ እንዳለው የማይካድራውን የሟጮች ቁጥር በትክክል ለማወቅ አልቻልኩም ብሏል፡፡
ኢዜማ ወደ ስፍራው በማቅናት አደረኩት ባለው ማጣራትም የተለያዩ የጅምላ መቃብሮችን ማግኘቱን ያስታወቀ ሲሆን በዚህም በግፍ የተጨፈጨፉ ዜጎች አስክሬን በጅምላ መቀበሩ ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ መቸገሩን አስታውቋል፡፡
በወቅቱ የሟቾቹ አስክሬን በዶዘር በመቀበሩ ትክክለኛውን ቁጥር ለማወቅ ሁኔታውን ውስብስብ እንዳደረገው ነው ኢዜማ ያስታወቀው፡፡
በአሁኑ ሰዓት በማይካዳራ የሚኖሩ ነዋሪዎች የፀጥታ ስጋት አለብን ያሉም ሲሆን በአካባቢው የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ንግድ ሱቆችና ተመሳሳይ ተቋማት ላይ ያልተቋረጠ ዘረፋ መቀጠሉን በምልከታ ወቅት የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረውኛል ብሏል ኢዜማ፡፡
እንዲሁም በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ላይ ዝርፊያ እየተፈፀመ ይገኛል ሲልም አስታውቋል፡፡
ነዋሪዎቹ የሱዳን ጦር ሊመታን ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸውና ሳምሪ የተባለው ህገወጥ ቡድን ሙሉ በሙሉ መወገዱን እርግጠኛ አይደለንም ብለውኛል ሲል ፓርቲው በሰጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በየአካባቢው ተቆርጦ የቀረው የህወሃት ታጣቂ ቡድን ባልታሰበ ጊዜና ሁኔታም ጥቃት ሊፈፅምብን ይችላል የሚል ስጋትም እንዳላቸውም በመግለጫው ተጠቅሷል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ.ም











