ብሔራዊ የደም ባንክ ባለፉት ስድስት ወራት ከ146 ሺህ በላይ ከረጢት ደም መሰብሰቡን ገለፀ፡፡

ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት በአገር አቀፍ ደረጃ ከ146 ሺህ በላይ ከረጢት ደም ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ሰበስቤያለሁ ብሏል። ባለፈው ግማሽ አመት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ44 ሺህ በላይ ከረጢት ደም ከበጎ ፈቃድ ደም ለጋሾች ማግኘቱን ገልጿል።

ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በ12 ወራት ውስጥ 343 ሺህ ከረጢት ደም ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች መሰብሰብ አቅዶ ነበር።ይሁንና ተቋሙ በ6 ወራት ውስጥ 146 ሺህ 451 ከረጢት ደም መሰብሰቡን ገልጿል፡፡ የህብረተሰቡ በፈቃደኝነት ደም የመለገስ ልምድ እያደገ በመምጣቱ በግማሽ ዓመት 85 በመቶ የዕቅድ አፈጻጸም ማሳካቱን ገልጿል።

በብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት፣ የደንበኞች የደም አሰባሰብ ሀላፊ ዶክተር ተመስገን አበጀ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 65 ዓመት ድረስ ያሉ ሰዎች ደም ቢለግሱ የዜጎችን ህይወት ከመታደግ ባሻገር ለራሳቸውም ጤንነት ጠቃሚ ነው ብለዋል።

አንድ ሰው ደም በሚለግስበት ወቅት አሮጌው የደም ህዋስ በአዲስ የሚተካ በመሆኑ ከደም ጋር በተያያዘ ከሚፈጠር ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት መዳን እንደሚቻልም በባለሙያዎች ይመከራል፡፡

በዳንኤል መላኩ
የካቲት 5 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.