በአዲስ አበባ በ49 ሚሊዮን ብር ወጪ የመረጃ ቋት ሊገነባ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሳኝ ኩነት መረጃና ምዝገባ ኤጀንሲ ከ49 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የራሱን የመረጃ ቋት ሊገነባ መሆኑን ገልጿል፡፡

ይህ የመረጃ ቋት መገንባትም ኤጀንሲው ከዚህ ቀደም የነበረበትን የሲስተም መቆራረጥ ችግር ይፈታል ተብሎለታል፡፡

በኤጀንሲው በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይም በተገልጋይ ዘንድ የሚታየውን እንግልት ያስቀራል ተብሏል፡፡

የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳሬክተርና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ሃላፊ አቶ መሃመድ አብድራሂም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት ኤጀንሲው ለፕሮጀክቱ 49 ነጥብ 6 ሚሊዬን ብር በመመደብ የራሱን የመረጃ ማዕከል ለመገንባት ወደ ስራ ገብቷል፡፡

የመረጃ ማከማቻ ቋት እና የሰነድ ማከማቻ ግንባታን እውን ለማድረግም ኤጄንሲው ባወጣው ግልፅ ጨረታ መሰረት አሸናፊ የሆነው ከነራ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ስራውን ተረክቦ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ቴክኖሎጂውን ወደ ስራ ለማስገባት ከስምምነት ላይ መደረሱን ነግረውናል፡፡

የግንባታ ስራው ሲጠናቀቅም ኤጀንሲው እስካሁን የነበረውን የኔትወርክ መቆራረጥ ከማስቀረቱም በላይ መረጃዎችን በሶፍትና በሀርድ ኮፒ ለመያዝና ዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት ፤ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠትና የህዝብ እርካታ ለማምጣት እንደሚያስችል ነግረውናል ።

ይህ የመረጃ ቋት መገንባትም ኤጀንሲው ከዚህ ቀደም የነበረበትን የሲስተም መቆራረጥ ችግር ይፈታዋል ተብሎለታል፡፡

በኤጀንሲው በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይም በተገልጋይ ዘንድ የሚታየውን እንግልት ያስቀራል ተብሏል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *