አንቶኒዮ ፋዉቺ ለሳይንስ ጥብቅና የቆሙ በሚል 1 ሚሊዮን ዶላር ተሸለሙ፡፡

አሜሪካዊዉ የተላላፊ በሽታዎች ምሁር አንቶኒዮ ፋዉቺ የኮሮና ወረርሽኝን በመከላከል ዙሪያ ከቀድሞዉ የአሜሪካ ፕሬዝዳት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ሲወዛገቡ ቆይተዋል፡፡

በዚህም ፋዉቺ ትራምፕ በሚሉት መሰረት ሳይሆን የሚሰጡት ምክርና ማብራሪያ በሳይንስ ላይ የተመሰረተ እንደነበር ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡

ፋዉቺ የቫይረሱን አደገኛነትና አሜሪካን ሊያስከፍላት የሚችለዉን ዋጋ አበክረዉ ወትዉተዋል፡፡

ለዚህ አበርክቷቸዉም በእስራኤል የሚሰጠዉ የዳን-ዴቪድ ዓመታዊ የ1 ሚሊዮን ዶላር ሽልማትን ለሳይንስ ጥብቅና የቆሙ ምሁር በሚል ተሸልመዋል፡፡

የ80 ዓመቱ የተላላፊ በሽታዎች ምሁር ፋዉቺ፣ የኮቪድ 19 ክትባቶች እንዲዘጋጁ ቅስቀሳና ድጋፍ እንዲሁም በኤች አይ ቪ ዙሪያ ለሚያደርጉት ምርምርም እዉቅና ተቸሯቸዋል፡፡

አንቶኒዮ ፋዉቺ በጤናዉ ዘርፍ ለሰባት የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች አማካሪ ሆነዉ መስራታቸዉንም ዘገባዉ ጠቁሟል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
የካቲት 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.