ሰብዓዊነትና ፍቅር ለትግራይና መትከል በሚል የተቋቋመው የእርዳታ አሰባሳቢ ኮሚቴ እና አለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ልዩ የእርዳታ ማሰበሰቢያ መርሃግሮችን አስታውቀዋል።

ይህም በመላው ሀገራችን የሚገኙ ዜጎች በሙሉ የሚችሉትን እርዳታ እንዲያደርጉ በሚል በ6 ክፍሎች በመመደብና እንዲሰባሰቡ በማደረግ እንደሆነ ኮሚቴው አስታውቋል።

በዚህም መሰረት፡-

1) የሃይማኖት ተቋማትን የካቲት 13 እና 14 2013 ዓ.ም
2)አትሌቶችና የስፖርት ቤተሰቦችን ሰኞ የካቲት 15 2013 ዓ.ም
3) የኪነጥበብ ባለሙያዎችን ማክሰኞ የካቲት 16/2013 ዓ.ም
4) ባለሃብቶችን ረቡዕ የካቲት 17/2013 ዓ.ም
5) የመንግስት ሃላፊዎችን ሃሙስ የካቲት 18/2013 ዓ.ም እንዲሁም
6) የመከላከያና የፀጥታ ክፍል ሃላፊዎችንና ሰራተኞችን አርብ የካቲት 19/2013 ዓ.ም በሚል መመደቡን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም የካቲት 20 እና 21 ደግሞ ህጻናትና ቤተሰቦች እንዲሁም የተቀሩትን የህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሰባሰቡ በማድረግ የተቻላቸውን ያህል እርዳታ እንዲያደርጉ ኮሚቴው ጥሪ አቅርቧል።

የኮሚቴው ሊቀመንበር የሆነዉ አርቲስትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ ባስተላለፈዉ መልእክት ለእኛው ወገን አኛው ደራሽ እስከሆንን ድረስ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የተለመደውን እርዳታ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡

የእርዳታ ማሰባሰቢያ ቦታዉ ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል መሆኑም ተገልጿል፡፡

በጅብሪል ሙሃመድ
የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *