በአሜሪካ በተከሰተ ከፍተኛ ቅዝቃዜ የ20 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በሃገሪቱ በተለያዩ ከተሞች የተከሰተዉ የአየር ቅዝቃዜ ከ25 ዓመታት ወዲህ አጋጥሞ አያዉቅም ተብሏል፡፡

በሚኒሶታ እስከ -39፣በሰሜን ዳኮታ እስከ -26 እንዲሁም በነብራስካ እስከ -30 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሚደርስ ቅዝቃዜ ተመዝግቧል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በነዚህ አካባቢዎች የተከሰተ አዉሎ ነፋስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ምንም አይነት የሃይል አቅርቦት እንዳያገኙ አድርጓቸዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

በዚህም በትንሹ 20 ሰዎች በቅዝቃዜ ምክንያት ለሞት መዳረጋቸዉን ስካይ ኒዉስ ዘግቧል፡፡

በሂዉስተን ያጋጠመዉን ቅዝቃዜ ለመቋቋም እሳት ሲጠቀሙ የነበሩ 4 የአንድ ቤተሰብ አባላት ደግሞ ቤታቸዉ ተቃጥሎ ለሞት መዳረጋቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የአሜሪካ ብሄራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት እንዳለዉ 100 ሚሊዮን የሚሆኑ አሜሪካዊያን ክረምቱን ተከትሎ ለሚከሰት የአዉሎ ነፋስ አደጋ የተጋለጡ ናቸዉ ሲል ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ቅዝቃዜዉ በአካባቢዉ እየተሰጠ የሚገኘዉ የኮሮና ቫይረስ ክትባት እንዲዘገይም ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፕሬዝዳንት ጆ-ባይደንም በዚህ ችግር ዉስጥ የሚገኙ ዜጎችን በአፋጣኝ የሃይል አቅርቦት እንዲያገኙ ለማድረግ መንግስታቸዉ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *