በአዉሮፓ ህብረት የንግድ አጋርነት አሜሪካ በቻይና ብልጫ ተወስዶባታል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተጽዕኖ በቶሎ ያገገመችዉ ቻይና ከአዉሮፓ ሀገራት ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊ ትስስር እያጠናከረች ትገኛለች፡፡

አሜሪካ በበላይነት ተቆጣጥረዉ በቆየችዉ የህብረቱ የንግድ ግንኙነት አሁን ዋና የንግድ ዘዋሪዋ ቻይና ሆናለች፡፡

ቻይና በፈረንጆቹ 2020 ከህብረቱ አባል ሀገራት ጋር ያደረገችዉ የንግድ ልዉዉጥ 709 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የአሜሪካ በአንጻሩ 671 ቢሊዮን ዶላር ነዉ፡፡

ይህም አሜሪካ የ 38 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ብልጫ በቻይና ተወስዶባታል፡፡

ተሽከርካሪዎች፣የህክምና መሳሪያዎችና የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ቻይና ወደ አዉሮፓ በብዛት የላከቻቸዉ ምርቶች መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

እንደ ሲ ኤን ቢ ሲ ዘገባ ባለፈዉ የፈረንጆቹ ዓመት 2020 የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተቋቁሞ የተሻለ ኢኮኖሚያዊ እድገት በማስመዝገብ ቻይና ቀዳሚ ሀገር ናት፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *