በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት በነዳጅ ላይ የታየውን የዋጋ ጭማሪ ከግምት በማስገባት የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ የታሪፍ ማሻሻያውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የታሪፍ ማሻሻያው የነዋሪውን የኑሮ ሁኔታ ከግምት በማስገባት በሚኒ ባስ፣ ሃይገርና መካከለኛ አውቶብሶች ላይ የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር ስጦታው አከለ ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሰረት በሚድ ባስ ወይም የሃይገርና መካከለኛ አውቶብሶች ላይ የተሻሻለው ታሪፍ እስከ 8 ኪሎሜትር 3 ብር የነበረው ባለበት የሚቀጥል ሲሆን ከ8 ኪ.ሜትር በላይ ያሉት ታሪፎች ላይ የ1 ብር ጭማሪ ተገርጓል።

በሚኒ ባስ ኮድ 1–3ን በተመለከት እስከ 2.5 ኪ.ሜ 2 ብር የነበረው ባለበት ይቀጥላል ተብሏል።

ከ 2.6 እስከ 5 ኪ.ሜ 4 ብር የነበረው 4.50 ብር ከ5.1 እስከ 7.5 ኪ.ሜ 6ብር የነበረው
6.50 ብር ከ7.6– 10 ኪሜ 8 ብር የነበረው 9 ብር
ከ10.1 -12.5 ኪሜ 10 ብር የነበረው 11 ብር ከ12.6- 15 ኪሜ 12 ብር የነበረው 13 ብር
ከ15.1 – 17.5 ኪሜ 13 ብር የነበረው 15.50 እንዲሁም ከ17.6 -20 ኪሜ 15- 17.50 ብር ሆኗል።

በሸገር አንበሳ እና ድጋፍ ሰጪ የብዙሃን ትራንስፖርቶች ላይ የከተማ አስተዳደሩ በአመት 1.5 ቢሊየን ብር ድጎማ በማድረግ በነበሩበት ዋጋ እንዲቀጥሉ ተደርጓል።

በጅብሪል ሙሐመድ
የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *