የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ ኢንጅነር ስጦታው አካለ በከተማዋ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።
ሃላፊው በዚህ ጊዜ እንዳሉት መኪናዎቹ መንግስት ባመቻቸው እድል መሰረት ከቀረጥ ነጻ የገቡ ሲሆን ባለቤቶች በቅድሚያ 20 በመቶውን ከፍለው ቀሪው 80 በመቶውን ደግሞ በረዥም ጊዜ ክፍያ ይፈፀማል።
መኪናዎቹን ለባለቤቶቹ አስረክበው ውል የማፈራራም ስነ ስርአቱ ተፈጽሟል ብለዋል።
መኪናዎቹ በሃገራችን የትራንስፖር ሴክተሩን ለማዘመን የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ብለዋል።
መኪናዎቹ የነዳጅ ፍጆታቸው ከነበሩት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ በመሆኑ በአካባቢ አየር ብክለትን ለመቀነስ ይረዳሉ ተብሏል።
በሀገራችን የትራንስፖርት እንቅስቃሴን በማቀላጠፍ በከፍተኛ መጠን የሚደረሰውን አደጋ ከመቀነስ ባለፈ የአዲስ አበባ ከተማን ውበትንና ገፅታዋን ለማጉላት ይጠቅማሉ ብለዋል።
እነዚህ መኪናዎችን ለማምረትና ለማስረከብ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ በብድር በተገኘ በጀት መሆኑንም ሀላፊው በመግለጫቸው ጠቁመዋል።
ባለ ላዳ ታክሲዎቹ በ4 ወራት ውስጥ በአዳዲሶቹ መኪናዎቻቸው አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩም ተገልጿል።
በጅብሪል ሙሐመድ
የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም











