ኢዜማ በቢሾፍቱ ለሞተው አባሉ መታሰቢያ ሐውልት መስሪያ ቦታ እንዲሰጠው ጠየቀ።

የኢዜማ የቢሾፍቱ ከተማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት ግርማ ሞገስ ለገሰ የካቲት 7 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት በተተኮሰባቸው ጥይት ሕይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ነው።

ፓርቲው በዚህ ጊዜ እንዳለው በቢሾፍቱ ከተማ የፖለቲካ እንቅስቃሴያችንን የሚያውኩ ተግባራት ይደርሱብን ነበር ብሏል።

ከዚህ በፊትም በቢሾፍቱ ችግሮች ይገጥሙን ነበር ከከተማው ነዋሪዎች ጋርም ስብሰባ ለማድረግ አስበን በከተማወ አስተዳደር ምክንያት አልተሳካልንም ብሏል ፓርቲው።

ፖሊስ ሟች የኢዜማ አባል መሆኑን አላውቅም ብሎ ለመንግስት ሚዲያዎች ክዷል ያለው ኢዜማ ይህ ግን ሀሰት ነው ሟች ግርማ ሞገስ የኢዜማ አባል መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት ከከተማው ሀላፊዎችና ከፖሊስ አመራሮች ጋር ይገናኝ ነበር ብሏል።

ለሟች ግርማ መታሰቢያ በከተማው ሀውልት የምንሰራበት ቦታ ይስጠን ሲልም ፓርቲው በመግለጫው ጠይቋል።

መንግስትም ጉዳዩን እንዲያወግዝ የጠየቀው ኢዜማ የከተማው ፖሊስ ወንጀሉን ተራ ግድያ ለማስመሰል እየሞከረ ነውም ብሏል።

በመቅደላዊት ደረጃ
የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *