በአማራ ክልል ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ ብቻ ሰርግ ላይ በተተኮሰ የደስደስ ጥይት የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።

ሰርግ ላይ አላግባብ በሚተኮስ ጥይት የሰው ህይወት እየጠፋ መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ አስታውቋል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ አምስት ወረዳወች ላይ ብቻ ከጥር 30/05/2013 ዓ.ም እስከ የካቲት 08/06/2013 ዓ/ም ባለው ጊዜ በሰርግ ላይ ለደስታ መግለጫ በሚል የጦር መሳሪያ ተኩስ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል።

እንዲሁም በ8 ሰዎች ላይ ደግሞ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

ተጠርጣሪወችም በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑንም ፖሊስ ገልጿል።

በሰርግ እና በልዩ ልዩ ኘሮግራሞች ላይ በመጠጥ በሚፈጠር ሞቅታ እና በጦር መሳሪያ አጠቃቀም እንዝህላልነት ምክንያት በሚያሳዝን ሁኔታ በተደጋጋሚ የሰው ህይወት እየጠፋ በመሆኑ ህዝቡ ከእንዲህ አይነቱ ወንጀል እራሱንና ቤተሰቡን ለመጠበቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል።

ድርጊቱን የሚፈጽሙ ህገወጦችን ለፖሊስ በመጠቆም ትብብር እንዲያደርግ መልዕክትም አስተላልፈዋል ፖሊስ፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን
የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *