ማክሮን ከሚመረተዉ የኮቪድ 19 ክትባት ዉስጥ ከ 4 እስከ 5 በመቶ የሚሆነዉ ለድሃ ሀገራት ይሰጥ የሚል ፕሮፖዛል አቅርበዋል፡፡

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን፣ፕሮፖዛሉን ለአዉሮፓ ህብረት አባል ሀገራትና ለአሜሪካ ነዉ ማቅረባቸዉ የተነገረዉ፡፡

ይህን ክትባት በፍትሃዊነት ማሰራጨትና በጋራ መጠቀም ካልተቻለ፣ የሃገራትን ኢ-ፍትሃዊነት አስተሳሰብና ድርጊት የሚያጋልጥ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

አብዛኞቹ የኮቪድ-19 ክትባቶች የሚገኙት በበለጸጉ ሀገራት እጅ መሆኑን የገለጹት ማክሮን እነዚህ ሀገራት ድሃ ሀገራትን ታሳቢ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

ማክሮን የጀርመኗ መራሂተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል የኮቪድ-19 ክትባት በፍትሃዊ መልኩ እንዲዳረስ እያደረጉት ላለዉ ጥረትም አመስግነዋል፡፡

አሜሪካ በበኩሏ ኮ-ቫክስ የተባለዉ ክትባት በፍትሃዊነት እንዲሰራጭ 4 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጓን አስታዉቃለች፡፡

ማክሮን ቻይናና ሩሲያም ክትባቱን በፍትሃዊ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የሚሰራዉን ስራ ሊያግዙ ይገባል ነዉ ያሉት፡፡

በዓለምአቀፍ ደረጃ እዉቅና ተሰጥቷቸዉ እየተመረቱ ከሚገኙ የኮቪድ-19 ክትባቶች ዉስጥ 75 በመቶ የሚሆነዉ ያለዉ በ10 ሀገራት እጅ ነዉ፡፡

ፋይናንሽያል ታይምስ

በሙሉቀን አሰፋ
የካቲት 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *