የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሳወቀው የኮሌጁ የኩላሊት ህክምና ክፍል ሀላፊ የነበሩት ዶክተር ሞሚና ሙሀመድ ከሀገር የወጡት በስምምነትና ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ነው ብሏል።
የኮሌጁ የአካዳሚክ ጉባኤው በሚፈቅደው መሰረት ለሁለት አመት ከደሞዝ ነጻ ለማገልገል ነው የወጡት ተብሏል።
ዶክተር ሞሚና ተመልሰው ሲመጡም በኮሌጁ ስራቸውን እንደሚቀጥሉ ሰምተናል።
ዶክተር ሞሚና የኩላሊት ህክምና ክፍሉ መስራች መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ከ10 በላይ ባለሙያዎችንም አፍርተዋል።
ዜናው ሲሰማ በህብረተሰቡ ዘንድ የተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል ሊፈጠር ይችል ይሆን ወይ የሚል ስጋት እንደማይኖር ኮሌጁ አሳውቋል።
እንደ አለም ጤና ድርጅት መረጃ በኢትዮጵያ ከ10ሺ ሰዎች 3ቱ የኩላሊት በሽታ ተጠቂ ናቸው።
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2008 አ.ም የኩላሊት ንቅለ ተከላ መደረጉ ይታወሳል።
በመቅደላዊት ደረጀ
የካቲት 12 ቀን 2013 ዓ.ም











