ሶሪያ በየቀኑ 140 ሺ በርሜል በላይ ነዳጅ በአሜሪካ እየተዘረፍኩ ነዉ አለች፡፡

በሶሪያ በእንግሊዝኛዉ ምህጻረ ቃሉ SDF ወይም የሶሪያ ዲሞክራሲያዊ ሃይል የሚባል ታጣቂ ቡድን አለ::

ይህ ታጣቂ ቡድን ደግሞ ከፍተኛ ድጋፍ የሚደረግለት በአሜሪካ ነዉ፡፡

ታጣቂ ቡድኑ በአሁኑ ወቅት ከተቆጣጠራቸዉ አካባቢዎች በየቀኑ ከ140 ሺ በርሜል በላይ ነዳጅ ወደ ኢራቅ በህገ-ወጥ መንገድ እያጓጓዘ መሆኑን የሃሳካህ ገዥዉ ጋሳን ሃሊም ካህሊል ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ ወታደሮችን ከተለያዩ ሀገራት ማስወጣት ከሚለዉ መርሃቸዉ በተቃራኒዉ በዚህ አካባቢ ወታደሮችን ሲያሰማሩ መቆየታቸዉንና በአሁኑ ወቅት የሶሪያ ነዳጅ በህገ-ወጥ መንገድ እየተጓዘ ወደ ኢራቅ እየተወሰደ መሆኑን ፕረስ ቲቪ ዘግቧል፡፡

ታጣቂዎችን አሜሪካ በእጅ አዙር እየተጠቀመችባቸዉ መሆኑንም ባለስልጣኑ ተናግረዋል፡፡
በየቀኑም በአማካይ ከ140 ሺ በርሜል በላይ ነዳጅ ከሃገር እንደሚወጣ ጠቁመዋል፡፡

ፔንታጎን በበኩሉ ተዘረፈ ስለተባለዉ ነዳጅ የማዉቀዉ ነገር የለም፤ወታደሮች በአካባዉ እንዲሰማሩ የተደረገዉ ግን የታቅፊር ታጣቂዎች በአካባቢዉ ባሉ መሰረተ-ልማቶች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ለመጠበቅ ነዉ ብሏል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *