በኢትዮጵያ 123 የብሌን ንቅለ ተከላ ተደረገ።

ባለፉት 12 ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ የአይን ባንክ 123 የአይን ንቅለ ተከላ መደረጉ ተነግሯል።

የአይን ባንክ ዳይሬክተር ወ/ሮ ለምለም አየለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ባለፉት 12 ወራት ውስጥ 123 ሰዎች አይን ብሌን ንቅለ ተከላ ተደርጎላቸዋል ብለዋል።

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአይን ባንኩ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያደረገ ቢሆንም ንቅለ ተከላውን ለማድረግ ተችሏል ብለዋል ዳይሬክተሯ።

በተለያዩ ምክንያቶች የሚጣሉ የአይን ብሌኖች ቢኖሩም 180 የአይን ብሌን ልገሳ መደረጉን ሰምተናል።

የብሌን ልገሳውና ብሌን ንቅለ ተከላው ከሌሎች ጊዜያት ጋር ሲነጻጸር እጅግ ያነሰ ሆኖ ተመዝግቧል።

ይህም የሆነው በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት አለም አቀፍ መመሪያዎች እስኪወጡ ድረስ ለተወሰኑ ወራት የብሌን ማንሳት ስራውን ቆሞ እንደነበር ተገልጿል።

አሁን ላይ ያለው የብሌን ልገሳ ግንዛቤ የተሻሻለ ቢሆንም አሁንም ግን ከሀይማኖት ጋር የሚያገናኙት ሰዎች ስላሉ የበለጠ መስራት እንዳለብን ያሳል ሲሉ ወ/ሮ ለምለም ተናግረዋል።

የካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ብፁህ ካርዲናል ብርሀነ እየሱስ ከሰሞኑ የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል መግባታቸው ትልቅ ማስተማሪያ ይሆናል ተብሏል።

ባንኩ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 18 አመታት 2 ሺህ 523 የአይን ብሌን ንቅለ ተከላ መከናወኑንም ከተቋሙ ሰምተናል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።

በመቅደላዊት ደረጀ
የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *