በዲሞክራቲክ ኮንጎ የጣሊያን አምባሳደር መገደላቸዉ ተገለጸ፡፡

የጣሊያን መንግስት እንዳስታወቀዉ በዲሞክራቲክ ኮንጎ የአገሪቱ አምባሳደር የነበሩት ሉካ አታናሲዮ በተባበሩት መንግስታት ተሽከራካሪ ዉስጥ ሆነዉ በመጓዝ ላይ ሳሉ በተፈፀመባቸዉ ጥቃት ህይዎታቸዉ አልፏል ብሏል፡፡

ከአምባሳደሩ በተጨሪም አብረዋቸዉ ሲጓዙ የነበሩ ፖሊሶች መሞታቸዉን አልጄዚራ የጣሊያንን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

አምባሳደር አታናሲዮ እና የፀጥታ ሃይሎቹ በጋራ በመሆን በተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ግብረ ሃይል ተልዕኮ ተሸከርካሪ በመጓዝ ላይ ሳሉ መገደላቻዉም ታዉቋል፡፡

ለጥቃቱ እስካሁን ሓላፊነት የወሰደ አካል ባይኖርም ጥቃቱ በተፈፀመበት የአገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል ተደጋጋሚ ጥቃቶች መድረሳቸዉን ዘገባዉ አስታዉሷል፡፡

የአገሪቱ መንግስት እንዳስታወቀዉ አምባሳደሩ ከ2017 ጀምሮ አገራቸዉን ወክለዉ በዲሞክራቲክ ኮንጎ ተልዕኮ ላይ ይገኙ ነበር ብሏል፡፡

በአባቱ መረቀ
የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *