የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ባዕድ ነገሮችን መለየት የሚያስችሉ ዘመናዊ የፍተሻ ማሽኖችን መተግበር ጀመረ።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እና በቀጠሮ ማረፊያ ቤት የተለያዩ ዘመናዊ የፍተሻ ማሽኖችን ወደ ስራ ማስገባቱን ተቋሙ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ጌጅ ኤክስራይ እና ወክ ስሩ የተባሉ የፍተሻ ማሽኖችን ነው ወደ ስራ ማስገባቱን ያስታወቀው፡፡

ወደ ስራ የገቡት እነዚህ ማሽኖች ለማረም ማነጽ ሥራ ተቀባይነት የሌላቸው ይልቁንም ስነ ልቦናዊም ሆነ አካላዊ ጉዳት የሚያስከትሉ ባዕድ ነገሮች በታራሚ ጠያቂ ቤተሰቦች አማካኝነት የሚገቡ ነገሮችን በቀላሉ መለየት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

እንደዚሁም ከምግብ ጋር ተቀላቅለው ወይም በአካል ተደብቀው ወደ ማረሚያ ቤት ሊገቡ የሚችሉ ነገሮችን በቀላሉ ለመቆጣጠር ተብሎ የተዘጋጀ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ዘመናዊ የፍተሻ ማሽኖች የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽንን የሪፎርም ሂደት እየተፈታተነ የሚገኘውን ህገ ወጥ እና የተከለከሉ ነገሮች ወደ ታራሚዎች እንዳይገቡ ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራር ነው ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከቴክኖሎጅው ጋር አብረው መራመድ የሚችሉና ለሙያው ቅርብ የሆኑ አባሎችን በመለየት እና ስልጠና በመስጠት በሌሎች ቀሪ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ማዕከላትም በተያዘው የበጀት ዓመት የቴክኖሎጅው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሰራል ብሏል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.