20 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመውን እጣ አሸናፊ እድለኛ እንደጠፋበት ብሔራዊ ሎተሪ አስታወቀ።

ጳጉሜ አምስት ቀን 2012 ዓ.ም የወጣው 20 ሚሊየን ብር የሚያሸልመው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ እጣ አሸናፊ አልታወቀም ተብሏል፡፡

የእጣ ቁጥሩ ከወጣ ከአምስት ወራቶች በላይ ቢያስቆጥርም አሸናፊ ሆኖ የቀረበ እና ሽልማቱን የወሰደ ግለሰብ የለም ተብሏል፡፡

ጳጉሜ አምስት ቀን የወጣው የ20 ሚሊየን ብር አሸናፊ የእጣ ቁጥር 0216884 እንደነበረ ይታወቃል፡፡

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የሎተሪው አሸናፊ እስከ መጋቢት አንድ ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብቻ ከመጣ ብሩን መውሰድ ይችላል ብሏል።

ከ1ኛ እጣ አሸናፊ የሆኑ እድለኞች ብራቸውን እንደወሰዱ ከተቋሙ ሰምተናል።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በአዲስ መልክ ለሁለት ተከታታይ ጊዜ የ20 ሚሊየን ብር የእጣ አዘጋጅቶ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ለመጀመርያ ጊዜ ያቀረበው 20 ሚሊየን ብር የሚያሸልመው እጣ በጊዜው ለአሸናፊው ማስረከቡም አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 15 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *