በኢኳዶር ማረሚያ ቤት በተቀሰቀሰ ግጭት የ50 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በአገሪቱ ሶስት ከተሞች በተቀጣጠለው የማረሚያ ቤት ተቃውሞ ከሟቾች በተጨማሪም በርካታ ዜጎች እንደተጎዱም ታውቋል።

የግጭቱ መንስኤ በሁለት ተቀናቃኝ እስረኞቾ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነ ያስታወቀው የአገሪቱ ፖሊስ ተቃውሞውን ለማረጋጋት የፀጥታ አካላት መመደባቸው ተነግሯል።

የኢኳዶሩ ፕሬዚዳንት ሌኒን ሞሬኖ አመፀኞች በፈጠሩት ግጭት አገሪቱን ለማተራመስ ሞክረዋል ነገር ግን በሁሉም አካባቢዎች የፀጥታ አካላትን አሰማርተናል ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአገሪቱ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች አመፀኞች በሚፈጥሩት ግጭት ዜጎች ህይወታቸውን እያጡ እንደሆነም ዘገባው አስታውሷል ።

እንደ ፖሊስ መረጃ ከሆነም በማረሚያ ቤቶች ግጭት እንዲንቀሰቀስ በእስር ላይ የሚገኙ የፀጥታ እና ደህንነት ሰዎች እንደሚሰሩም ታውቋል።

በአባቱ መረቀ
የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *