በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን መስሪያ ቤት ታመመ በተባለው አንድ ሰራተኛ ምክንያት ባለጉዳዮች እየተጉላሉ መሆኑን ተናገሩ።

የተሽከርካሪ የፍጥነት መገደቢያን በተመለከተ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን መስርያ ቤት አገልግሎት የሚፈልጉ ባለ ጉዳዮች አገልግሎቱን ማግኘት እንዳልቻሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ቅሬታ አቅርበዋል፡፡

የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች እንደሚሉትም ከሆነ ከተሽከርካሪ የፍጥነት መገደቢያ ጋር በተያያዘ ደብዳቤ ላይ የሚመታልን መሃተም ቢኖርም ከባለስልጣኑ መስርያ ቤት ግን ይህን አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ምክንያቱን ብንጠይቅም ያገኘነው ምላሽ ማህተብ የሚያደርገው ሰው ታሟል የሚል ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የፌደራል ትራንስፖርት ባለ ስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ይግዛው ዳኘው የችግሩን መፈጠር አምነው ተገልጋዩ እንዲያውቀው ጉዳዩን በባለስልጣኑ መስርያ ቤት ማስታወቂያ ለጥፈናል ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ቦታው ላይ በሃላፊነት የተቀመጡት ሰው በህመም ምክንያት አገልግሎት መስጠት ባለመቻላቸው ነው ብለውናል፡፡

ታዲያ እሳቸው ወደ ስራ ገበታቸው እስኪመለሱ ሌላ ሰው አይሽፍንም ወይ ስንል ለጠየቅናቸው ጥያቄ ሌላ ሰው ለመተካት ውክልና ያስፈልጋል ሲሉ ነግረውናል፡፡

አገልግሎቱ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ማለትም ከ9 ቀን በኋላ እንደሚጀምር ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.