ኳታር የአለም ዋንጫ ዝግጅት በምትገነባው ስታዲየሞች ምክንያት 6ሺህ አምስት መቶ ዜጎች ህይወት ማለፉ ተምማ።

ኳታር ለ2022 ለምታዘጋጀው የአለም ዋንጫ በምትገነባቸው ስታድየሞች ላይ እስካሁን 6 ሺህ 500 ሰራተኞች ሞተዋል ተብሏል፡፡

ይህ ማለት ደግሞ በየሳምንቱ 12 ሰራተኞች ግንባታው ላይ ህይወታቸውን ያጣሉ እንደማለት ነው፡፡

ዘ ጋርዲያን ይዞት የወጣው አስደንጋጭ ዘገባ በመላው አለም ድንጋጤን የፈጠረ ዜና ሆኗል፡፡

ኳታር የስታድየሞቹ ግንባታ ከጀመረች ወዲህ በርካታ ቁጥር ያለው ስደተኛ በግንባታ ስራ ላይ ማሰማራቷ አይዘነጋም፡፡

ይህ ዘገባ ያለፈውን የፈረንጆቹ 2020 አመት የማቾች ቁጥር መረጃ አልተካተተበትም ነው የተባለው፡፡

ከሟቾቹ መካከል የህንድ የፓኪስታን የኔፓል የባንግላዲሽ እና የሲሪላክና ዜግነት ያላቸው ስደተኞች ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ ነው ዘጋርዲያን ያተተው፡፡

እነዚህ ሰራተኞች ለሞት የተዳረጉበት ዋነኛ ምክንያት ለሰራተኞቹ የሚደረገው ጥንቃቄ እጅጉን አነስተኛ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *