የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከስፖርት አወራራጅ ቤቶች 50 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

አስተዳደሩ ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ካሉ 42 የስፖርት አወራራጅ ቤቶች 50 ሚሊዮን ብር ገቢ አግኝቻለሁ ብሏል።

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶች ገቢያቸው ለመቆጣጠር የሚያስችል መመርያ እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል፡፡

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት በኢትዮጵያ 42 የሚደርሱ የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶች አሉ።

በመሆኑም አስተዳድሩ የነዚህን አወራራጅ የቁማር ድርጅቶች ገቢያቸው በተገቢው መንገድ ለመቆጣጠር መመርያ እየተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ በህጋዊ መንገድ በስፖርት ውድድር ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ 42 የስፖርት ውድድር ቤቶች ይገኛሉም ብለዋል፡፡

እነዚህ የስፖርት አወራራጅ ቤቶች በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የሚገኙ በመሆናቸው ገቢያቸው ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ሆኖ መገኘቱ ተገልጿል፡፡

ህጋዊ የስራ ፍቃድ ኖሯቸው ገቢያቸው የት እንደሚገባ እና የት እንደሚደርስ አይታወቅም ያሉት አቶ ቴዎድሮስ መመርያው ይህንን ችግር የሚፈታ ነው ብለዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በየሆቴል ቤቶች እና በየመንደሩ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ ፍቃድ ሳያገኙ በሎተሪ ሽያጭ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በተለያዩ ጊዜያት ጥረት ቢደረግም ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንዳልቻሉ ነው የተነገረው፡፡

እንደዚሁም የህግ አካላት እነዚህን ግለሰቦች የጀመሩትን ህገወጥ የሎተሪ ሽያጭ እንዲያስቀሩ ትዕዛዝ ብናስተላልፍም ሊተባበሩን አልቻሉም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *