በአዲስ አበባ ዘመናዊ የአየር ጥራት መለኪያ መሳሪያ ሊተከል ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አካበቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን አማካሪ የሆኑት አቶ ጥበቡ አሰፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፁት፣ ኮሚሽኑ ከC40s (የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የተቋቋሙ ትልልቅ የአለም ከተማዎች ህብረት) ጋር በመተባበር የአየር ጥራት መለኪያ መሳሪያ ሊተከል ነው ብለዋል።

በከተማዋ ከ8 በላይ የአየር ጥራት መቆጣጠሪያ መሳሪዎች በስራ ላይ ሲሆኑ አሁን ደግሞ አንድ ተጨማሪ የአየር ጥራት መለኪያ መሳሪያ እንደሚተከል ተገልጿል።

መሳሪያው የአየር ጥራትን ከመለካት በተጨማሪ ሌሎች የአየር ጥራት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን ስራቸውን ለመከታተል የሚያስችል ነው ብለዋል።

እንዲሁም በከተማዋ በየቀኑ ያለውን የአየር ፀባይ ቀድሞ በመተንበይ ቅድመ ጥንቃቄዎችን ለመውሰድ ይረዳል ብለዋል።

በዋናነት ግን በከተማዋ ያለው አየር ፀባይ መበከሉንና አለበከሉን በማመላከት ለከተማዋ ማህበረሰብ ለጤና ተስማሚ የሆነውን የአየር ፀባይ ለመለየት ያገለግላል ሲሉም ገልፀውልናል።

በጅብሪል ሙሀመድ
የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *