የኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ኤጀንሲ በ26 ከተሞች የውሀ ፍተሻ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ።

ከሁለት አመት በፊት ደሴና ወላይታ ሶዶ ከተሞች የከርሰ ምድር ውሀ በኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ኤጀንሲ ተፈትሾ ጥራቱ መረጋገጡ ይፋ ተደርጎ ነበር።

በተያዘው አመት ደግሞ በ26 ከተሞች የውሀ ፍተሻ ሊደረግ መሆኑን የኤጀንሲው የኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አቤል አንበርብር ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ሶስት አይነት የውሀ ደረጃ መመዘኛዎች አሉ የሚሉት አቶ አቤል ውሀን መፈተሽ አስገዳጅ ቢሆንም የተግባሩ መዘግየት እንዳለ ይናገራሉ።

እኛ በሙሉ የፍተሻ አቅም እያለን ግን አስፈጻሚና ተቆጣጣሪው አካል ማስተግበር ባለመቻሉ የሚፈጠረው የጥራት ችግር ያሳስበናልም ብለዋል።

ምንም እንኳን የዘገየ ቢሆንም በትላንትናው ዕለት ከከፍተኛ የውሀ ሀብት ሀላፊዎች ጋር ውይይት መደረጉም ተገልጿል።

ዜጋው በየቤቱ የሚደርሰውን ውሀ በልበ ሙሉነት እንዲጠቀም የውሀ ፍተሻ ማድረግ ወሳኝ ነው ተብሏል።

ከ5 አመት በፊት አንድም የታሸገ ውሀ ደረጃውን ያሟላ አልነበረም ያሉት የኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተሩ አሁን ላይ ግን ሁሉም የታሸጉ ውሀዎች የጥራት ደረጃቸው ሳይረጋገጥ ወደ ገበያ አይወጡም ብለዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በመቅደላዊት ደረጀ
የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *