የአማዞን ደን በህገ-ወጥ መንገድ ፌስ ቡክ ላይ ለሽያጭ መቅረቡ ብዙዎችን አስገርሟል፡፡

የዓለማችን ዋና እስትንፋስ ነዉ በሚል የሚገለጸዉ የአማዞንን ደን ሻጭ ነን የሚሉ ወገኖች ብቅ ብለዋል፡፡

በደቡባዊ አሜሪካ የሚገኘዉ የዓለማችን ታላቁ ጥቅጥቅ ደን አማዞን፣ከዚህ ቀደም በተከሰተበት ተደጋጋሚ የእሳት አደጋ በርካታ የደኑ ክፍል መጎዳቱ ይነገራል፡፡

አሁን ደግሞ በተለይም በብራዚል አካባቢ የሚገኘዉ የደኑ ክፍል ፌስቡክ ላይ በህገ-ወጥ መንገድ ለሽያጭ እየቀረበ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ይህን የሚያደርጉ ሰዎች ደግሞ ትክክለኛ የይዞታ ባለቤትነት መብት የሌላቸዉ መሆናቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ፌስቡክ በዚህ ዙሪያ ተጠይቆ በሰጠዉ ምላሽ፣ ይህ በኔ ብቻ የሚፈታ ችግር ባለመሆኑ ከአካባቢዉ ገዥዎች ጋር እመክርበታለሁ ማለቱ ተሰምቷል፡፡

በፌስቡክ ላይ የግዙኝ ማስታወቂያ እየተላለፈ ያለዉ የደኑ ክፍል በትንሹ አንድ ሽህ የእግር ኳስ ሜዳዎች ያህል ስፋት ያለዉ መሆኑም ተነግሯል፡፡

አካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰሩ ዓለማቀፍ ተቋማት በበኩላቸዉ በዚህ ድርጊት ላይ የብራዚል መንግስት እጅ አለበት በሚል የቦልሶናሮን አስተዳደር እየተቹ ነዉ፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *