በሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሀይል ዘጠኝ የአልሸባብ ወታደሮችን ገደለ።

የአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ ኃይሎች ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው አሸባሪዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተነግሯል፡፡

የአልቃይዳ ፅንፈኛ ቡድን ተባባሪ ነው የሚባለው የአልሻባብ የሽብር ቡድን ላይ ትናንት ጠዋት በሀገሪቱ ደቡብ ምዕራብ በሚገኘው የጦር ሰፈሩ ላይ ጥቃት በመሰንዘር ቢያንስ ዘጠኝ ወታደሮች መገደላቸውን አናዶሉ የዜና ወኪል ዘግቧል ፡፡

በቤይ ክልል ቃሻህደረ ከተማ የወረዳው ምክትል ኮሚሽነር ሞሃመድ ሙክታር በአፍሪቃ ህብረት ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ ኃይል (አሚሶም) በሚያገለግሉ የኢትዮጵያ ወታደሮች የተደገፈው ጦር ቢያንስ 9 አሸባሪዎችን መገደሉን ለአከባቢው መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል ፡፡

በዚህ ጥቃት ከሞቱት በተጨማሪ ከ11 በላይ የአሸባሪ ቡድኑ ተዋጊዎች ቆስለው መሳሪያዎቻቸውን መማራካቸው መረጃው አክሏል፡፡

ቃሻህደረ ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ደቡብ ምዕራብ 346 ኪሎ ሜትር (214 ማይል) ርቃ የምትገኝ እና ቤይ ዋና ከተማ ከሆነችው ከባይዶዋ በስተ ምዕራብ 90 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ የእርሻ ከተማ ናት ፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *