በአዲስ አበባ ለኮቪድ 19 ፅኑ ህሙማን የሚያስፈልጉ መተንፈሻ የተገጠመላቸው የማሽን አልጋዎች ሙሉ በሙሉ መያዛቸው ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ለኮቪድ 19 አገልግሎት የሚውሉት በተለይም ፅኑ ህሙማን የሚጠቀሙባቸው የማሽን አልጋዎች ሙሉ በሙሉ መያዛቸው ተነግሯል፡፡

በአዲስ አበባ ለዚህ አገልግሎት እየዋሉ ያሉት የማሽን አልጋዎች ወይንም mechanical ventilator የተገጠመላቸው አልጋዎች 65 ብቻ ናቸው፡፡

ለዚህ ማሽን የሚያስፈልጉ ግብአቶች ውድ መሆንና በቀላሉ ያለመገኘት ሁኔውን በእጅጉ ፈታኝ እንደሚያደርገውም ሰምተናል፡፡

በጤና ሚኒስትር የክሊኒካል ሰርቪስ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ያዕቆብ ሰማን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት የመተንፈሻ ማሽን ወይንም mechanical ventilator የተገጠመላቸው አልጋዎች ሙሉ በሙሉ በህሙማን ተይዘዋል፡፡

በአጠቃላይ በሃገሪቱ ለዚህ አገልግሎት የሚውሉ አልጋዎች ቁጥር ከ 645 እንደማይዘል የነገሩን አቶ ያእቆብ ለሌሎች አገልግሎት እየዋሉ ከሚገኙት የማሽን አልጋዎች ውጪ ለኮሮና ቫይረስ ፅኑ ህሙማን የሚያስፈልጉት የማሽን አልጋዎች በተለይም በአዲስ አበባ የሚገኙት ሙሉ በሙሉ ተይዘዋል፡፡

በሃገሪቱ የሚገኙ የኦክስጅን አልጋዎች እጥረት አላጋጠመንም ያሉን አቶ ያእቆብ ነገር ግን በማሽን ለመቆየት የሚገደዱ የፅኑ ህሙማን ታካሚዎች በየእለቱ ቁጥሩ ማሻቀቡና ያሉት አልጋዎች ያለመመጣጠን፤ ህብረተሰቡም ሆነ በተለይም ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ለቫይረሱ እያሳዩት ያለውን መዘናጋት እና ቸልተኝነት ጉዳዩን ውስብስብ እንዳደረገው ነግረውናል፡፡

ስለሆነም ትኩረት ቢሰጡበትና በቫይረሱ ምክንያት የሚሞተውን የሰው ልጆች ህይወትንም መታደግ ብንችል መልካም ነው ብለውናል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *